Message From Berue Head

Message From Berue Head

የክልሉ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በአዋጅ ከተሰጡት ተግባርና ኃላፊነት መካከል መንግሥት ከተለያዩ የገቢ ምንጮች የሚሰበስበውን ሀብት የሚያስተዳደርና እና ወጪውን የሚቆጣጠር ሲሆን ከሴክተር እስከ ወረዳ ድረስ የመንግሥት ሀብት የሚመራባቸዉ የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር የህግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀትና አፈጻጸሙን በመከታተል፣ ለልማት አስፈላጊ የሆነውን በጀት ለመሠረታዊ አገልግሎቶች እንዲውል ጥራትና ፍትሃዊነትን ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ያስተገብራል፡፡

መንግስት አገራዊ ኢኮኖሚውን ለማሳደግና የሕዝቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የረጅም፣የመካከለኛና የአጭር ጊዜ ፕሮግራሞች በማዘጋጀትና እና ፕሮጀክቶች በማቀድ በሥራ ላይ የሚያውል ሲሆን አፈጻጸማቸውም የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን ቢሮው ዘመናዊ የመንግስት የሂሳብ አያያዝና የጥሬ ገንዘብ አስተዳደር በመዘርጋት ፣የመንግስትን ሀብት ከብክነት ለመከላከል የሚያስችል ጠንካራ የውስጥ ኦዲት ቁጥጥር በማድረግ ፣ግልጽና ውጤታማ የሆነ የግዥና የንብረት አስተዳደር ስርዓት ከማስፈን፤ የፋይናንስ ስራውን የሚደግፍ ዘመናዊ የመረጃ ስርዓት ከመዘርጋት እና አሰራሩን ከማጠናከር አኳያ በርካታ ስራዎችን መስራት ላይ ነው ።

በተጨማሪም የክልሉ መንግስት ከልማት አጋር ድርጅቶች የሚያገኘውን ሀብት አፈጻጸምን በመከታተል በኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ዘርፍ የተሰማሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የክትትልና ድጋፍ ስራ በማከናወን ይገኛል።

በክልላችንን የፋይናንስ ግልጽነትና፣ ተጠያቂነትንና ፍትሃዊነት እንዲሰፍና ለኢኮኖሚ ዕድገት አጋዥ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካል ወጪ ቆጣቢ የሆነ የበጀት ስርአትን በመከተልና ብክነትን በመቀነስ የሚመደበው በጀት ለታለመለት አላማ እንዲውል በማድረግ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።

Mohammed Yahya | Head

Recent News

RECENT NEWS DELIVERED FROM US TO YOU

Recent Blogs

BLOGS FROM US TO YOU

FAQs

OUR ANSWERS FOR THE MOST QUESTIONS WE GET

What financial assistance programs are available for residents in need?
What are the penalties for late tax payments?
What types of financial reports are available to the public?

Our Office Location

HAVE SOMETHING TO SAY OR NEED ADDITIONAL INFORMATION? DROP BY TO OUR OFFICE

Contact Us

You Can Contact Us Through Our Main Phone Line! : 011-155-26-80